የፓርላማ አባል በሽንት ቤት ውስጥ ለ13 ሰዓታት ተቆልፎባቸው አደሩ

ADDIS_NEWSneutral2026-09-18 12:20:33 UTC
AdYour ad here[email protected]

የፓርላማ አባል በሽንት ቤት ውስጥ ለ13 ሰዓታት ተቆልፎባቸው አደሩ ​የቤልጂየም የፓርላማ አባል ፍሬደሪክ ኤረንስ በፓርላማው መጸዳጃ ቤት በር መቆለፊያ ብልሽት ምክንያት ተቆልፎባቸው ማደራቸው ተሰማ። ​ፓርላማ አባሉ ስልካቸውን ቢሯቸው ጠረጴዛ ላይ ትተው በመውጣታቸው እርዳታ ለመጠየቅ አልቻሉም። በሩን ቢደልቁም እና ቢጮሁም ድምፃቸውን የሚሰማቸው ሰው አልነበረም። ​በማግስቱ ጠዋት በጽዳት ሰራተኛ አማካኝነት የተገኙት ኤረንስ፣ ቦታው በቂ አየር የሌለው በመሆኑ የትንፋሽ እጥረት እና የማዞር ስሜት አጋጥሟቸዋል። በመሆኑም ከደረሰላቸው የህክምና እርዳታ በኋላ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። @Addis_News @Addis_News

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]