የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርቶችን ሳያሟሉ ለሚመዘገቡ ተማሪዎች ባለሥልጣኑ ማሳሰቢያ ሰጠ።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-09-18 12:27:02 UTC
AdYour ad here[email protected]

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርቶችን ሳያሟሉ ለሚመዘገቡ ተማሪዎች ባለሥልጣኑ ማሳሰቢያ ሰጠ። የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በቅድመ-ምረቃና በድህረ-ምረቃ መርሃ ግብሮች ለመመዝገብ የሚፈልጉ ተመዝጋቢዎች የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለባቸው አሳስቧል። ባለሥልጣኑ እንዳስታወቀው፣ የቅድመ-ምረቃ ተመዝጋቢዎች የትምህርት ሚኒስቴር ለትምህርት ዘመኑ ያሳወቀውን የከፍተኛ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ አሟልተው መገኘት ይጠበቅባቸዋል። ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የተመረቁ ባለሙያዎች በበኩላቸው፣ በሠለጠኑበት የሙያ መስክ በደረጃ 4 ወይም በቀድሞው 10+3 ወይም 12+2 ዲፕሎማ ያጠናቀቁ መሆን አለባቸው። በተጨማሪም በሙያቸው ደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ ምዘና (COC Level 4) ፈተና ወስደው ማለፋቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]