አካል ጉዳተኝነት ከውጤት ያልገደባት ተማሪ

TIKVAHUNIVERSITYneutral2026-09-18 15:09:20 UTC
AdYour ad here[email protected]

አካል ጉዳተኝነት ከውጤት ያልገደባት ተማሪ ‎ ተማሪ ሶሊያና ማሩ፣ ‎በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች መካከል አንዷ ናት። ‎ ‎የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዋ ሶሊያና፣ 437 ነጥብ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አሳክታለች። ‎ ‎አካል ጉዳተኛ ብትሆንም፣ አልችልም ብላ ተስፋ ሳትቆርጥ ፈተናዎችን ተሻግራ ከፍተኛ የሚባል ውጤት አስመዝግባለች። 👏👏 ላስመዘገበችው ውጤት የቤተሰቦቿ እና የመምህራን ልዩ ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳረገላት ትገልጻለች። ‎በዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ የሕግ ትምህርት ለመቀጠል ፍላጎት እንዳላት የምትገልፀው ተማሪ ሶሊያና፤ በኤሌክትሪክ የሚሠራ ዘመናዊ ዊልቼሮች ድጋፍ እንዲደረግላት ጠይቃለች። #አሚኮ @tikvahuniversity

Read the full story at tikvahuniversity ↗
AdYour ad here[email protected]