ኦነሠ-የጽምዶ አባል «አይደለሁም» አለ
ኦነሠ-የጽምዶ አባል «አይደለሁም» አለ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) የኢትዮጵያ መንግስትን በጋራ “ለመዉጋት” በተመሠረተዉ “ፅምዶ” በተባለዉ ህብረት ውስጥ ምንም ተሳትፎ እንደሌለውና የትብብሩ አባል አለመሆኑን አስታውቋል፡፡በትጥቅ ትግልና በተለያዩ መንገዶች የኢትዮጵያ መንግስትን ለመውጋት ተቋቋመ የተባለው ጽምዶ የውጪ ኃላትንም ጭምር ያሳተፈ ነው በሚል በኢትዮጵያ መንግስት ጭምር መገለጹ ይታወሳል፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) ዛሬ በ X ገጹ ባወጣው መግለጫ እንዳብራራው ግን “የኦነሠ እና ጽምዶን ግንኙነት አስመልክቶ የሚወራው ከእውነት የራቄ ነው” ብሏል፡፡ “ኦነሠ ጽምዶ በተባለ ትብብር ውስጥ የለም፤ ጉዳዩንም በቅርበት አይከታተል” ያለው መግለጫ፣ ነገር ግን “ከአገሪቱ ሰሜን አስከ ደቡብ እንዲሁም ከምስራቅ እና ምዕራብ ጫፍ ተቃዋሚዎችን ያቀፈ ትብብር ቅርጽ እየያዘ ነው”…
Read the full story at addis_reporter ↗