በጋምቤላ ክልል በሕዝብ ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ ጥቃት 10 ሰዎች ተገደሉ
በጋምቤላ ክልል በሕዝብ ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ ጥቃት 10 ሰዎች ተገደሉ በጋምቤላ ክልል ታጣቂዎች በሕዝብ ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ላይ ባደረሱት ጥቃት በትንሹ 10 ሰዎች ሲገደሉ፤ ሌሎች በርካቶች ቆሰሉ። ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ያደረሱት ትናንት መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ/ም መነሻቸውን ከጋምቤላ ከተማ አድርገው ወደ ኢታንግ ፣ ላረ እና ጅካዎ ወረዳዎች በመጓዝ ላይ ነበሩ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ መሆኑን የአይን ምስክሮች ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። በወታደራዊ አጀብ ይጓዙ እንደነበር የተገለጸው ስድስት ተሽከርካሪዎች አቦል ወረዳ ሲደርሱ ጥቃቱ መፈጸሙ ተሰምቷል። በደረሰው ጥቃት የሟቾች ቁጥር 16 ሊደርስ እንደሚችል የአይን ምስክሮች ተናግረዋል። የተጎጂዎችን ቁጥር ደግሞ 60 ያህል ሊሆኑ እንደሚችሉ የተናገሩም አሉ። ለበርካቶች ህይወት ህልፈት እና መቁሰል ምክንያት ለሆነው…
Read the full story at ayuzehabeshanews ↗