በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን መቀጠል የሚፈልጉ ነባር እና አዲስ ተማሪዎች ጉዳይ ከዩኒቨርሲቲዎቹ ጋር እየተመከረበት መሆኑ ተገለጸ።
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን መቀጠል የሚፈልጉ ነባር እና አዲስ ተማሪዎች ጉዳይ ከዩኒቨርሲቲዎቹ ጋር እየተመከረበት መሆኑ ተገለጸ። የትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ከክልሉ ውጭ ወዳሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ጥያቄ ያቀረቡ ተማሪዎችን በጊዜያዊነት የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ በቅርቡ እንደሚገለጽላቸው አስታውቋል። ሚኒስቴሩ በተለያየ ምክንያት በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን መቀጠል የሚፈልጉ ነባርና አዲስ ተማሪዎችን በሚመለከት ግን ከዩኒቨርሲቲዎቹ ጋር ውይይት እያደረገ መሆኑ ታውቋል። በትግራይ ክልል መቀጠል የሚፈልጉ ተማሪዎች የሚተላለፈውን ውሳኔ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ሚኒስቴሩ ጠይቋል። በተጨማሪም በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ተማሪዎች ሁኔታው ሲስተካከል መጀመሪያ ወደተመደቡባቸው በትግራይ ክልል…
Read the full story at tikvahethiopia ↗