የጉግል ምርት የሆነው «ጀሚኒ» ኤአይ የሦስት ኩባንያዎችን የሳይበር ደህንነት መጣሱ ተገለጸ።
የጉግል ምርት የሆነው «ጀሚኒ» ኤአይ የሦስት ኩባንያዎችን የሳይበር ደህንነት መጣሱ ተገለጸ። የጉግል የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሞዴል የሆነው "ጀሚኒ" የሳይበር ደህንነት ብቃቱ በሚፈተሽበት ወቅት ያለምንም የሰው ልጅ ትዕዛዝ በራሱ ተነሳሽነት የሦስት ኩባንያዎችን የደህንነት ከለላ ሰብሮ መግባቱን ዎልስትሪት ጆርናል መዘገቡን ተከትሎ የዕለቱ መነጋገሪያ ዜና ሆኗል። በግንቦት ወር በተካሄደው በዚህ ሙከራ ጀሚኒ ለሕዝብ ይፋ የሆኑ መረጃዎችን እና የይለፍ ቃላትን በመገመት ወደ ድረ-ገጾቹ የገባ ሲሆን፣ ድርጊቱን የፈጸመው ድረ-ገጾቹ የሙከራው አካል እንደሆኑ በማሰብ መሆኑን የጉግል የደኅንነት ክፍል ምክትል ፕሬዝዳንት ሄዘር አድኪንስ ገልጸዋል። የኤአይ ሞዴሉ ወደ ኩባንያዎቹ የመረጃ ሥርዓት ከገባ በኋላ በራሱ ውሳኔ እንቅስቃሴውን ማቆሙና ጉግል ጥቃቱ ለደረሰባቸው ተቋማት መረጃ መስጠቱንና ክስተቱም…
Read the full story at tikvahethmagazine ↗