አሜሪካ ለሶማሊያ ሰላም አስከባሪዎች የሚደረገው የሎጅስቲክስ ድጋፍ የሚቆምበትን ጊዜ አራዘመች

TIKVAHETHMAGAZINEneutral2026-09-19 16:15:46 UTC
AdYour ad here[email protected]

አሜሪካ ለሶማሊያ ሰላም አስከባሪዎች የሚደረገው የሎጅስቲክስ ድጋፍ የሚቆምበትን ጊዜ አራዘመች አሜሪካ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሶማሊያ ድጋፍ ቢሮ (UNSOS) በኩል ለአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ (AUSSOM) የሚደረገውን የሎጅስቲክስ ድጋፍ ለማቋረጥ የያዘችውን የጊዜ ገደብ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለማራዘም ተስማምታለች። አሜሪካ ለዲፕሎማቶች ባሰራጨችው ረቂቅ ሰነድ መሠረት፣ በሶማሊያ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የድጋፍ ቢሮ ለአንድ ዓመት በሚቆይ የደረጃ በደረጃ ቅነሳ ሂደት አልፎ ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ተስማምታለች። ይህ ውሳኔ ድጋፉ እ.ኤ.አ. በታህሳስ 2026 ማብቂያ ላይ በድንገት ይቋረጣል ተብሎ የተደቀነውን ስጋት ያስቀረ ነው ተብሏል። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋሺንግተን ወደፊት ቢሮውን ሥራ በገንዘብ እንደማትደግፍ ገልጸው፣…

Read the full story at tikvahethmagazine ↗
AdYour ad here[email protected]