የክልል መንግሥታት ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ እስከ 2% ሊቆርጡ ነው።
የክልል መንግሥታት ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ እስከ 2% ሊቆርጡ ነው። የክልል መንግሥታት ከሠራተኞች ወርሃዊ ደመወዝ ላይ ከ0.5 እስከ 2 በመቶ የሚደርስ የአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ፈንድ መዋጮ የሚቆርጡበትን አሠራር መዘርጋታቸው ተሰማ። ይህ ከሠራተኞች ደመወዝ የሚቆረጥ መዋጮ በረቂቅ ደረጃ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ በመጨረሻ በጸደቀው የኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር አዋጅ ላይ ቀሪ መደረጉ ይታወሳል። ይሁን እንጂ አብዛኞቹ ክልሎች ተመሳሳይ የመዋጮ መጠን ለመሰብሰብ የወሰኑ ሲሆን፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግን ከሁሉም ከፍ ያለ ማለትም ከ1 እስከ 2 በመቶ ለመቁረጥ ወስኗል። @Addis_News @Addis_News
Read the full story at addis_news ↗