ሰቨን ስታር ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ 849 በመጀመሪያ ዲግሪ እና በቴክኒክና ሙያ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

TIKVAHUNIVERSITYneutral2026-09-20 11:50:36 UTC
AdYour ad here[email protected]

ሰቨን ስታር ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ 849 በመጀመሪያ ዲግሪ እና በቴክኒክና ሙያ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ 560 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞች የተመረቁ ሲሆን፣ 447 በጤና ፕሮግራሞች እና 113 በቢዝነስ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው። ቀሪዎቹ 289 ተማሪዎች በደረጃ አራት በቴክኒክና ሙያ ፕሮግራሞች የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል። ከአጠቃላይ ተመራቂዎቹ መካከል 2/3ኛ የሚሆኑት የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ ናቸው። በቴክኒክ እና ሙያ ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ሦስት ተማሪዎች ነፃ የዲግሪ ፕሮግራማቸውን በኮሌጁ እንዲቀጥሉ ዕድል የተሰጠ ሲሆን፣ በተመሳሳን በዲግሪ ፕሮግራም ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ሦስት ተመራቂዎች በኮሌጁ የሥራ ዕድል እንደተመቻቸላቸው በምረቃ መርሐግብሩ ወቅት ተገልጿል። @tikvahuniversity

Read the full story at tikvahuniversity ↗
AdYour ad here[email protected]