በኢትዮጵያ “አካታች የሽግግር መንግስት” ለመመስረት ያለመ የሰባት አማጽያን ኃይሎች እና የፖለቲካ ድርጅቶች ትብብር መመስረቱ ይፋ ተደረገ።
በኢትዮጵያ “አካታች የሽግግር መንግስት” ለመመስረት ያለመ የሰባት አማጽያን ኃይሎች እና የፖለቲካ ድርጅቶች ትብብር መመስረቱ ይፋ ተደረገ። “የኢትዮጵያ ህዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለህልውና” የሚል ስያሜ የተሰጠውን ይህን ትብብር ከመሰረቱት ውስጥ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)፣ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነሰ) እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እንደሚገኙበት ተገልጿል። ይህ የተገለጸው ዛሬ እሁድ መስከረም 10፤ 2019 በትግራይ ክልል በሚገኙ ዜና ማሰራጫዎች በኩል በተላለፈ መግለጫ ነው። መግለጫውን በንባብ ያቀረቡት በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው አማጺ ቡድን አፋብንን በሊቀመንበርነት የሚመሩት አቶ ዘመነ ካሴ ናቸው። አቶ ዘመነ “ትብብር ለህልውና” የሚል አጭር መጠሪያ የሚጠቀመው የጋራ ትብብር ሰብሳቢ መሆናቸውም በቪዲዮ በተሰራጨው መግለጫ ላይ ተመልክቷል። የእዚሁ…
Read the full story at addis_news ↗