"ለደቡብ ሱዳን ፈቅጃለሁ ትገንባ" ግብፅ

WASULIFEneutral2026-09-21 09:46:51 UTC
AdYour ad here[email protected]

"ለደቡብ ሱዳን ፈቅጃለሁ ትገንባ" ግብፅ ግብፅ በደቡብ ሱዳን የታቀደውን የውሃ ግድብ ግንባታ የቴክኒክ ግምገማዎችን ካካሄደች በኋላ መስማማቷን የሀገሪቱ የውሃ ሀብትና መስኖ ሚኒስትር ሀኒ ሴዊላም አስታወቁ። ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ ከደቡብ ሱዳን የቀረቡት የቴክኒክ ጥናቶችና ሰነዶች ከተመረመሩ በኋላ የግድቡ በግብፅ የውሃ ድርሻ ላይ የሚያደርሰው ተፅዕኖ “በጣም አነስተኛ” እና ሊተዳደር የሚችል መሆኑ ተረጋግጧል ብለዋል። ይህ ፕሮጀክት በናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ ማዕቀፍ ውስጥ ከቀረቡት 36 የውሃ ፕሮጀክቶች አንዱ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ግብፅ ከደቡብ ተፋሰስ ሀገራት ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥልም ሚኒስትሩ አብራርተዋል። ይህ 1 ቀን ብቻ ቀረው ​👇 https://yekinlibochaward.org/nominees/wasu-mohammed

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]