በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ እየተከታትልኩ ነው - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ እየተከታትልኩ ነው - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየመን ለሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊው ክትትል እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በየመን መንግሥት ኃይሎችና በኢራን በሚደገፉት የሑቲ ታጣቂዎች መካከል እየተካሄደ ባለው ውጊያ በርካታ ዜጎች ከየመን ወደ ጅቡቲ እየተሰደዱ መሆናቸውን የሚወጡ መረጃዎች አመልክተዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ መረጃም በሀገሪቱ ከሚገኙና ከተመዘገቡ ስደተኞች መካከል ትውልደ ኢትዮጵያውያን በርካታ እንደሆኑ ገልጿል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ፣ የእስያና ፓሲፊክ ሀገራት ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ደዋኖ ከድር ሚኒስቴሩ በየመን በሥጋት ውስጥ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በአካባቢው ያለው ሁኔታ አስቸጋሪ…
Read the full story at addis_news ↗