" አሽከርካሪዎቹ ሕይወታቸው ሳያልፍ በቤተሰቦቻቸው ጥረት በሰላም ተለቀዋል " - ማህበሩ

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-09-21 20:59:31 UTC
AdYour ad here[email protected]

" አሽከርካሪዎቹ ሕይወታቸው ሳያልፍ በቤተሰቦቻቸው ጥረት በሰላም ተለቀዋል " - ማህበሩ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ከተማ "ቢላ" በሚባለው አካባቢ ከሳምንት በፊት በርካታ ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች በታጣቂዎች ጥቃት ሲቃጠሉ፣ ታግተው ተወስደው የነበሩ አሽከርካሪዎች ከእገታ መለቀቃቸውን የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። የእገታና የቃጠሎ ጥቃቱ የተፈጸመው ጳጉሜ 1/2018 ዓ/ም ሲሆን፣ ጉዳዩን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ማብራሪያ የሰጠን ማህበሩ፣ ሾፌሮቹን "በተኩስ ነው ያስቋሟቸው፤ ተሽከርካሪዎቹ ተቃጥለዋል፤ ታጣቂዎቹ አምልጠዋል" ብሎ፣ ዲያው ስልክ ተደውሎለት ጉዳዩን ለሚመለከተው የመንግስት አካል እንዳሳወቀ ገልጾልን ነበር። ጥቃቱ በተፈጸመበት ቦታ ከነበሩት አሽከርካሪዎች መካከል የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች እንዳሉበት፣ አንዱ ሹፌር…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]