"ከንቲባው በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ነው ያረፈው። ሾፌሩ ግን የመኪና አደጋ በተከሰተበት እለት ወዲያው ነው ሕይወቱ ያለፈው" - አቶ ኃይሉ አዱኛ

ZENA24NOWneutral2026-09-22 19:06:37 UTC
AdYour ad here[email protected]

"ከንቲባው በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ነው ያረፈው። ሾፌሩ ግን የመኪና አደጋ በተከሰተበት እለት ወዲያው ነው ሕይወቱ ያለፈው" - አቶ ኃይሉ አዱኛ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን መተሃራ ከተማ፥ የከተማው ከንቲባና አሽከርካሪ ባጋጠማቸው ድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወታቸው ማለፉን የአካባቢው ነዋሪ እና የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። አንድ የአካባቢው ነዋሪ እንደነገሩንና ከአካባቢው በወጡ መረጃዎች መሰረት፣ የመተሃራ ከተማ ከንቲባ አቶ አዲሱ ዋቆ እና አንድ ሹፌር በደረሰባቸው ድንገተኛ የመኪና አደጋ ሕይወታቸው አልፏል። ነዋሪው የሞታቸው ምክንያት ሲያስረዱ፣ "የመኪና አደጋ ነው፤ አረጋግጫለሁ። ከንቲባው አቶ አዲሱ ዋቆ ይባላል፤ በጣም ጥሩ ሰው ነበር። ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ/ም ነበር የመኪና አደጋው የደረሰው 'ኢላላ' አካባቢ ከሹፌሩ ጋር እየተጓዙ በነበረበት…

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]