የትኩስ ሻይ ቡና አፍቃሪዎች ማወቅ ያለባቸው እውነታ
የትኩስ ሻይ ቡና አፍቃሪዎች ማወቅ ያለባቸው እውነታ በጣም ትኩስ ሻይ ወይም ቡና መጠጣት ለጉሮሮ ካንሰር ሊያጋልጥ እንደሚችል በቅርቡ የተደረገ ጥናት አረጋገጠ። ተመራማሪዎች እንዳሉት ከ10 ዓመታት በላይ ባደረጉት ክትትል፣ ትኩስ መጠጥ አዘውትረው የሚጠጡ ሰዎች ከቀዝቃዛ መጠጥ ተጠቃሚዎች ጋር ሲወዳደሩ እስከ ሦስት እጥፍ የሚደርስ የስጋት ደረጃ አላቸው። ከዚህም በላይ በቀን ከስድስት ሲኒ በላይ መጠጣት አደጋውን ይጨምረዋል። ችግሩ ያለው ከሻይ ወይም ከቡና ዓይነት ሳይሆን ከመጠጡ ከፍተኛ ሙቀት የተነሳ ነው። መፍትሔው ቀላል ነው፤ ሙቅ መጠጦችን ትንሽ እስኪቀዘቅዙ መጠበቅ ከዚህ ስጋት ይጠብቃል። ተመራማሪዎቹ 1 ሚሊዮን ገደማ በሚደርሱ አዋቂዎች ላይ ጥናቱን ማድረጋቸውን ዲስካቨር ማጋዚን ጠቁሟል፡፡ @Seledadotio @Seledadotio
Read the full story at addis_news ↗