የፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አዲስ መጽሐፍ ተመረቀ
የፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አዲስ መጽሐፍ ተመረቀ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሕይወት ታሪክ እና ወታደራዊ ጀግንነት የሚያሳይ «ድል ቁርሱ» የተሰኘው መጽሐፍ ተመረቀ። መጽሐፉ የግለሰብ ታሪክ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ከገጠሬዋ ኢትዮጵያ ክፍል ተነስቶ የወታደራዊ ሕይወትን በመቀላቀል ሀገር በፈተና ማዕበል በተናጠችበት ወቅት በፅናት የቆመ ታላቅ መሪን መንፈስ የሚያሳይ እና የሕይወት ውጣ ውረድን በጥልቀት የሚያስቃኝ መሆኑን የመንግሥት ሚዲያ ዘግቧል፡፡ በዚሁ የመጽሐፍ ምርቃት ሥነ-ሥርዓት ላይ ፕሮፌሰር ዳኛቸው አስፋ፣ የአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ ዳይሬክተር አቶ ዛዲግ አብራሃ እንዲሁም አቶ ብርሃኑ ደቦጭ በመጽሐፉ ላይ ምሁራዊ ሂስና ዳሰሳ አቅርበዋል፡፡ በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ…
Read the full story at addis_news ↗