ኢሠማኮ የመንግሥት ኃላፊዎች ምላሽ ባለመስጠታቸው መማረሩን ገለጸ‼️
ኢሠማኮ የመንግሥት ኃላፊዎች ምላሽ ባለመስጠታቸው መማረሩን ገለጸ‼️ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሠማኮ) አሠሪና ሠራተኛን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ አብዛኛዎቹ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ምላሽ ባለመስጠታቸው ምክንያት ቅሬታውን አቀረበ። የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ እንዳሉት፣ በርካታ የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎች ለደብዳቤ፣ ለስልክ ጥሪም ሆነ ለመልእክት ምላሽ አይሰጡም፤ እንዲሁም ሕግና መርህን መሠረት አድርገው ከመነጋገር ይልቅ በራቸውን ይዘጋሉ። ፕሬዚዳንቱ አክለውም "የኢንዱስትሪ ሰላሙ እንዳይናጋ ወዴት እንሂድ? ሁሉንም ነገር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መውሰድ አለብን ወይ?" በማለት ጠይቀዋል። አዎንታዊ ምላሽ የሚሰጡ ተቋማት የመንግሥት ኃላፊዎች ምላሽ የመንፈግ ችግር ቢኖርም፣ የግል ተቋማት ኃላፊዎች የተሻለ ምላሽ እንደሚሰጡ ኮንፌደሬሽኑ አስታውቋል።…
Read the full story at addis_reporter ↗