🇪🇹 ኢትዮጵያ አንድ ደረጃ አሻሻለች‼️
🇪🇹 ኢትዮጵያ አንድ ደረጃ አሻሻለች‼️ 🕊ኢትዮጵያ በተያዘው የአውሮፓዊያን ዓመት የዓለም አገራት የሰላም አመላካቾች ከ163 አገራት 138ኛ ደረጃ ተሠጣት። ኢትዮጵያ፣ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር፣ ዘንድሮ አንድ ደረጃ አሻሽላለች። 🕊 ለአገራት የሰላም ጠቋሚ ደረጃ የሚያወጣው ዓለማቀፉ የኢኮኖሚክስና ሰላም ኢንስቲትዩት፣ ከ5 ከያዘው ነጥብ ለኢትዮጵያ 2 ነጥብ 6 ነጥብ ሠጥቷታል። አገሪቱ ዝቅተኛ ነጥብ ያገኘችባቸው ጠቋሚዎች፣ ፖለቲካዊ ሽብር፣ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት፣ ከጎረቤት አገራት ጋር ያላት ግንኙነት፣ ውስጣዊ ግጭቶች፣ የውስጣዊ ግጭቶች አስከፊነት እና የአነስተኛ ጦር መሳሪያዎች ተደራሽነት ናቸው። 🕊ኢትዮጵያ በደረጃው ከተካተቱ 44 የአፍሪካ አገራት ያገኘችው 35ኛ ደረጃ ነው። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Read the full story at addis_reporter ↗