"ሕወሓት በአፋርና በአማራ ክልሎች ጥቃት ከፍቷል" አቶ ጌታቸው ረዳ
"ሕወሓት በአፋርና በአማራ ክልሎች ጥቃት ከፍቷል" አቶ ጌታቸው ረዳ የሕወሓት አመራር በአፋር እና በአማራ ክልሎች በሚገኙ የመንግሥት ይዞታዎች ላይ ማለዳ ላይ ሰፊ ጥቃት መክፈቱን አቶ ጌታቸው ረዳ አስታወቁ። የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ አማካሪ ሚንስትር አቶ ጌታቸው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጨምሮ በርካታ አካላት በትግራይ ሌላ ዙር ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ መቅረቱ አሳዛኝ ነው ብለዋል። በተጨማሪም ሕወሓት በትግራይ የሚገኙ የፌዴራል መንግሥት የሚቆጣጠራቸውን አውሮፕላን ማረፊያዎች መቆጣጠሩን ተከትሎ ወደ ትግራይ የሚደረጉ እና ከትግራይ የሚወጡ በረረራዎች መቋረጣቸውን ገልጸው፣ የሕወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራር ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ፈጽሟል ሲሉ ከሰዋል። #WasuMohammed…
Read the full story at wasulife ↗