“ማርገዝ“ የምትወደው የ14 ልጆች እናት

ADDIS_REPORTERneutral2026-09-23 11:02:26 UTC
AdYour ad here[email protected]

“ማርገዝ“ የምትወደው የ14 ልጆች እናት አፍሪካ አሜሪካዊት የሆነችው ካረን ዴሪኮ የ14 ልጆች እናት ስትሆን፣ ማርገዝ እጅግ እንደምትወድና ጤናዋ እስከፈቀደ ድረስ ተጨማሪ ልጆችን መውለድ እንደምትፈልግ በተደጋጋሚ ተናግራለች። ከ14 ልጆች በኋላም ቤተሰቧ ሙሉ እንዳልሆነ እንደሚሰማት ነው የምትናገረው፡፡ ይህ ከልክ ያለፈ የልጆች ፍላጎቷ ታዲያ ከባሏ ከዲዮን ዴሪኮ ጋር የነበራቸውን የ20 ዓመታት ትዳር እንዲፈርስ ምክንያት ሆኗል። ጥንዶቹ እ.ኤ.አ በሰኔ 2024 በይፋ ተፋተዋል። ይሁን እንጂ ከፍቺው በኋላም ሁለቱ የቀድሞ ጥንዶች ልጆቻቸውን በጋራ ለማሳደግ መስማማታቸውን ገልጸዋል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter

Read the full story at addis_reporter ↗
AdYour ad here[email protected]