በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የሚመራው የትግራይ ክልል መንግስት፤ በፌደራል መንግስት “ተከፈተብኝ” ያለውን “ወረራ” ለመመከት የክልሉን “ሰራዊት” “መመሪያ ሰጥቶ” ማሰማራቱን አስታወቀ።
በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የሚመራው የትግራይ ክልል መንግስት፤ በፌደራል መንግስት “ተከፈተብኝ” ያለውን “ወረራ” ለመመከት የክልሉን “ሰራዊት” “መመሪያ ሰጥቶ” ማሰማራቱን አስታወቀ። በክልሉ የሚካሄዱ የወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ ዘመቻዎችን እና ኦፕሬሽኖችን የሚመለከቱ መረጃዎችን፤ ከሚመለከተው አካል ውጪ ማሰራጨት “ህጋዊ ተጠያቂነት የሚያስከትል” መሆኑንም የክልሉ መንግስት አስጠንቅቋል። በፌደራል መንግስት ዕውቅና የተነፈገው በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የትግራይ ክልል መንግስት ይህንን ያስታወቀው፤ ዛሬ ረቡዕ መስከረም 13፤ 2019 ባወጣው መግለጫ ነው። የክልሉ መንግስት መግለጫውን ያወጣው፤ በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከትላንትና ጀምሮ “ጥቃቶች” እና “ውጊያዎች” እየተካሄዱ መሆኑ በተለያዩ የመረጃ ምንጮች ይፋ መደረጉን ተከትሎ ነው።…
Read the full story at addis_news ↗