#ጥቆማ
#ጥቆማ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በሰብአዊነት ትምህርት ቤቱ ለሚሰጠው የአጭር ጊዜ የሰርተፍኬት ስልጠና ማመልከቻ መቀበል ጀምሯል። ማህበሩ በሰብአዊነት እና በሰብአዊ መሪነትና ዲፕሎማሲ መስኮች ለሚሰጠው ለዚህ የሶስተኛ ዙር ስልጠና ከ60 የማይበልጡ ወጣት ተወዳዳሪዎችን እንደሚቀበል አስታውቋል። አመልካቾች ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ (BA/BSc) እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ እንዲሁም በሰብአዊ ስራ ለማገልገል ፍላጎት ያላቸው መሆን አለባቸው ተብሏል። ለሦስት ወራት በሚሰጠው ትምህርቱ በሳምንት ቢያንስ ሦስት ቀናት በአካል መገኘትን ይጠይቃል። ሥልጠናው ሙሉ በሙሉ #በነፃ የሚሰጥ ይሆናል። ከጥቅምት 25 እና 26 ቀን 2019 ዓ.ም. (በመደበኛ የስራ ሰዓት) በሳሪስ አደይ አበባ በሚገኘው የትምህርት ቤቱ ካምፓስ በአካል በመገኘት ማመልከት እንደሚቻልም ማኅበሩ አስታውቋል።…
Read the full story at tikvahethmagazine ↗