ትራምፕ የቻይናውን መሪ ሺ በደማቅ ስነ ስርአት ተቀበሉ።
ትራምፕ የቻይናውን መሪ ሺ በደማቅ ስነ ስርአት ተቀበሉ። የቻይናው መሪ ሺ ጂምፒንግ ለሶስት ቀናት ይፉዊ የስራ ጉብኝት ወደ ዋሺንግተን አቅንተዋል። ከአመታት በኋላ የተደረገው ይህ የሺ ጉብኝት፥ ዝግ ስብሰባዎች፣ የከፍተኛ አመራሮች የእራት ግብዣ እንደሚደረግበት ይጠበቃል። የኢራን ጦርነት፣ የታይዋን ጉዳት፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በሀገራቱ መካከል የከረረው የንግድ ጦርነት ዋነኛ የውይይት አጀንዳዎች ይሆናሉ። የትራምፕ አስተዳደር ባለፈው ረቡዕ በሀገራቱ ያለው የንግድ ስምምነት ለ11 ወራት መራዘሙን አስታውቀዋል። ይኸውም በታሪፍ መጨመር ለተወጠረው የንግድ ስርአት ጊዜያዊ እፎይታን ይሰጠዋል ተብሏል። የዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደህና መጣህ አቀባበል ከቀደሙት ጊዜያት ደመቅ ያለ መሆኑን ተከትሎ ፥ ስነስርዓቱ የበርካታ መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቧል። @Addis_News @Addis_News
Read the full story at addis_news ↗