Current Affairs

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-09-24 11:27:23 UTC
AdYour ad here[email protected]

Current Affairs በትግራይ ክልል፣ አዋሳኝ በሆኑት አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን እና በአፋር ክልል ኪልበቲ ረሱ ዞን አካባቢ ትላንት ውጊያ መቀስቀሱን ነዋሪዎች እና አመራሮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። 1. አፋር ክልል የአፋር ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሐመድ አሊ፣ " ሕወሓት ማክሰኞ ሌሊት የአፋር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል " ብለዋል። " በኪልበቲ ረሱ ዞን አብዓላ፣ መጋሌ፣ ወሰማ አካባቢዎች ጥቃት ከፍቷል። ቀድሞውኑ የፕሪቶሪያ ስምምነትን አፍርሰው እነርሱ ናቸው ጦርነት የከፈቱት " ሲሉ ከሰዋል። " በሰላም በተኙ ዜጎቻችን ላይ ጥቃት አድርሷል። ጦርነት ከፍቷል። በታላላቅ ከባድ መሳሪያዎች ጭምር ነው ጦርነት የከፈተው " ብለዋል። " እኛ እንደ ክልል ጦርነት አልፈለግንም። ሕወሓት ነው የአፋር ህዝብ ላይ ዳግም ጦርነት የከፈተው፤ ክልሉ የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]