ኢራን በኃይል አንገዛም ስትል ለድርድር በሩን ክፍት ማድረጓን አስታወቀች፡፡

ZENA24NOWneutral2026-09-24 12:01:02 UTC
AdYour ad here[email protected]

ኢራን በኃይል አንገዛም ስትል ለድርድር በሩን ክፍት ማድረጓን አስታወቀች፡፡ የኢራን ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ባደረጉት ንግግር፣ ኢራን በማስፈራራትና በኃይል ጫና የምትመራ አገር እንዳልሆነች አስታውቀዉ አሜሪካ የሰነዘረችውን የ“ማጥፋት” ማስፈራሪያ ተቃውመዋል። አክለውም ቴህራን “የኃይል ቋንቋን” እንደማትቀበል ገልጸዋል። በተመሳሳይ ግን ኢራን የጦርነቱን መቋጫ ለማምጣት ለውይይትና ለዲፕሎማሲ በሩን ክፍት ማድረጓን አሳውቃለች። በአሜሪካ በኩል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ ከኢራን ጋር የጦርነቱን መቋጫ የሚያመጣ ስምምነት ላይ ለመድረስ ረጅም የድርድር ሂደት እንደሚጠበቅ ገልጸዋል። ሆኖም ዋሽንግተን የዲፕሎማሲ አማራጩን ብቻ ሳይሆን የጦር አማራጯንም እንደምትጠብቅ አስጠንቅቀዋል፡፡ ይህም ሁለቱ ወገኖች ለውይይት ፈቃደኛ ቢሆኑም፣ በመካከላቸው…

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]