ፈርጣማዉ ዳኛ ለፍጥነታቸዉ ሲሉ ኪሎአቸዉን ቀንሰዋል
ፈርጣማዉ ዳኛ ለፍጥነታቸዉ ሲሉ ኪሎአቸዉን ቀንሰዋል በብራዚል ሊግ ዳኛ የሆኑት አንደርሰን ዳሮንኮ ከብራዚል ሊግ የዳኞች ኮሚቴ በቀረበላቸው ምክረ ሃሳብ ከሰዉነት ክብደታቸዉን ወደ 12 ኪሎግራም መቀነሳቸዉ ተዘግቧል። የአለማችን ፈርጣማዉ ዳኛ በመባል የሚታወቁት እኚህ የ 45 አመት አርቢትር ለፍጥነት እና ቅልጥፍና በሚል ነዉ ኪሎአቸዉን እንዲቀንሱ የታዘዙት። ዳኛዉም ለህልማቸዉ ሲሉ ኪሎአቸዉን ቀንሰዉ ጨዋታ መርተዋል። በርከት ያሉ የእግርኳስ ተመልካቾች በዳኛዉ የሰዉነት ቅርጽ መለወጥ ጥያቄ ፈጥሮባቸዉ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ አድረወገዉት ነበር። #ዳጉ_ጆርናል
Read the full story at zena24now ↗