መቀሌ እና አካባቢዋ በአብዝሃኛው ቦታ የኔትወርክ መቋረጡ ተሰምቷል።

WASULIFEneutral2026-09-24 20:45:12 UTC
AdYour ad here[email protected]

መቀሌ እና አካባቢዋ በአብዝሃኛው ቦታ የኔትወርክ መቋረጡ ተሰምቷል። ​በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ እና አካባቢው አሁን ምሽት የኢትዮ ቴሌኮም የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት በአብዝሃኛው መቋረጡ ተሰምቷል። ​ከስፍራው የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ የኔትወርክ መቋረጡ በከተማዋ ሙሉ በሙሉ ሳይሆን በአልፎ አልፎ እና በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ላይ የሚታይ ሲሆን፣ በአንጻሩ የሳፋሪኮም ኔትወርክ ግን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ​ይህ ችግር በመቀሌ ከተማ ብቻ ሳይወሰን ወታደሮች በሰፈሩባቸው ዞኖች እና ወረዳዎችም በተመሳሳይ መልኩ እንዳጋጠመ ተነግሯል። ከመቀሌ እና ከአካባቢው የተሰማው ይህ መረጃ በርካታ ዜጎችን አሳዝኗል።በዚህ ላይ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም። #WasuMohammed --------- ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የቴሌግራም…

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]