የቀድሞው የትግራይ ጊዚያዊ መስተዳድር ፕረዚደንት የነበሩት ጀነራል ታደሰ ወረደ በቁጥጥር ሥር ዋሉ
የቀድሞው የትግራይ ጊዚያዊ መስተዳድር ፕረዚደንት የነበሩት ጀነራል ታደሰ ወረደ በቁጥጥር ሥር ዋሉ የስልክ መስመር ከመቋረጡ በፊት የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ቤታቸው በህወሓት ቀታጣቂዎች ተከቦ መውጣትም መግባትም አይቻልም ነበረ። ጀነራል ታደሰ ወረደ የጊዚያዊ መንግስቱን እንዲመሩ በፌደራል መንግስት የስልጣን ጊዚያቸውን ለሁለተኛ ጊዜ ቢያራዝምላቸውም ለጦርነቱ ምክንያት ነው በተባለለት ምርጫ የተመረጠ «ጅምር መንግስት ወደ ስልጣን መልሻለሁ» ያለው ህወሓት እሳቸውን በሃይል አውርዶ በዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል መተካቱ ይታወሳል። ጀነራሉ ስለታሰሩበት ምክንያትም ሆነ ፍርድ ቤት መቅረብ አለመቅረባቸው የታወቀ ነገር የለም። ሌሎች የህወሓት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችም በቤታቸው ውስጥ በቁም መታሰራቸዉ አንዳንዶች ደግሞ ከሥራ መታገዳቸው መረጃዎች ያመላክታሉ። #ዳጉ_ጆርናል
Read the full story at zena24now ↗