" ... ወዴት እንሂድ ? ለማንስ አቤት እንበል ? " - አቶ ካሳሁን ፎሎ

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-09-25 20:04:06 UTC
AdYour ad here[email protected]

" ... ወዴት እንሂድ ? ለማንስ አቤት እንበል ? " - አቶ ካሳሁን ፎሎ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሠማኮ) በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳዮች ላይ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ከአንዳንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ምላሽ እንደማያገኝ ገለጸ። ኢሠመኮ እንደገለጸው፣ ለመንግሥት ተቋማት የሚጽፋቸው ደብዳቤዎች ምላሽ አያገኙም፤ ስልክ ሲደወልም ኃላፊዎች ስልካቸውን አያነሱም ፤ መልዕክት ሲላክም ምላሽ አይገኝም። የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ እንደተናገሩት፣ ለሠራተኞችና ለአሠሪዎች ጉዳይ ምላሽ መስጠት የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎች ግዴታ ነው። ነገር ግን አንዳንድ ባለስልጣናትና ኃላፊዎች ጉዳዮችን በእውነት፣ በመርህና በሕግ መሠረት ከመመለስ ይልቅ በራቸውን እንደሚዘጉ ገልጸዋል። " ይሆናልም አይሆንምም አይሉም፤ ለመነጋገርም በፍጹም አይፈልጉም " ሲሉ አቶ ካሳሁን ተናግረዋል። "…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]