ከትናንት ምሽት ጀምሮ በትግራይ እንዲቋረጥ የተደረገዉ የቴሌኮም አገልግሎት በሕወሓት ትዕዛዝ መሆኑ ተሰማ
ከትናንት ምሽት ጀምሮ በትግራይ እንዲቋረጥ የተደረገዉ የቴሌኮም አገልግሎት በሕወሓት ትዕዛዝ መሆኑ ተሰማ ሕወሃት፣ በትግራይ ክልል የኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎቶች እንዲቋረጡ ትዕዛዝ መስጠቱን ከታማኝ ምንጮች መስማቱን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘገበ። በክልሉ ከትናንት ሐሙስ ሌሊት ጀምሮ የኢትዮ ቴሌኮም የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ተቋርጠዋል። የኢንተርኔት ነጻነትን የሚከታተለው ኔት ብሎክስም፣ በክልሉ የኢንተርኔት አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ መስተጓጎሉን ገልጧል። ኾኖም ኢትዮ ቴሌኮምም ኾነ የትግራይ ባለሥልጣናት የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎቶች ለምን እንደተቋረጡ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ዛሬ ምሽት ድረስ ማብራሪያ አልሠጡም። #ዳጉ_ጆርናል
Read the full story at zena24now ↗