በኢትዮጵያ 58% ሴቶች ተገርዘዋል - ጥናት

ADDIS_NEWSneutral2026-09-26 10:35:06 UTC
AdYour ad here[email protected]

በኢትዮጵያ 58% ሴቶች ተገርዘዋል - ጥናት በኢትዮጵያ ከ15 እስከ 49 ዓመት ዕድሜ ውስጥ ካሉ ሴቶች መካከል 58 በመቶ የሚሆኑት የተገረዙ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ያወጣውን ጥናት ዋቢ በማድረግ ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል። የግርዛት መጠኑ በሶማሌ ክልል 94 በመቶ በመድረስ ከፍተኛው ሲሆን፣ በጋምቤላ ክልል ደግሞ 17 በመቶ በመሆን ዝቅተኛው ነው። አብዛኞቹ ሴቶች ከ5 ዓመት በታች ባለው ለጋ እድሜያቸው እንደሚገረዙና 5 በመቶ ያህሉ ደግሞ በሕክምና ባለሙያዎች እንደሚፈጸም ተጠቅሷል። በሌላ በኩል በህብረተሰቡ አመለካከት ላይ ጥሩ ለውጦች እየታዩ ነው፤ ወደ 80 በመቶ የሚሆኑ ሴቶችና ወንዶች ድርጊቱ ማቆም አለበት የሚል እምነት አላቸው። በተጨማሪም የሴቶች ማህበራት ቅንጅት ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር በኦሮሚያ፣ አማራና ሶማሌ ክልሎች የሴቶች ግርዛትና ያለ እድሜ ጋብቻን…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]