ሰበር ዜና ‼️ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አላማጣን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ወደ መኾኒ እየገሰገሰ ነው

NATNAELMEKONNEN21neutral2026-09-27 10:34:47 UTC
AdYour ad here[email protected]

ሰበር ዜና ‼️ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አላማጣን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ወደ መኾኒ እየገሰገሰ ነው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ትናንት የራያ አላማጣ አካባቢዎችን ከተቆጣጠረ በኋላ በዛሬው ዕለት አላማጣ ከተማን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ሥር በማድረግ ወደ መኾኒ ግስጋሴውን ቀጥሏል። በደረሰን መረጃ መሠረት፤ የአላማጣ ከተማ ከንቲባ ሞገስ ሽፈራው እና አስተዳዳሪው ዝናቡ ገብረመድህን ከተማዋን ለቀው ቀደም ብለው ወደ መኾኒ የሸሹ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ መኾኒንም ለቀው ወደ መቀሌ ማምራታቸው ተጠቅሷል። በተጨማሪም ከውጊያው የተረፉ የሕወሓት ታጣቂዎች በጋርጀለ እና በታኦ በኩል በመበታተን ማረፊያቸውን ወደ መኾኒ እና ማይጨው ማድረጋቸው ታውቋል።

Read the full story at natnaelmekonnen21 ↗
AdYour ad here[email protected]