ለመንግሥት ትምህርት ቤት መምህራን የደረጃ ዕድገት አዲስ መመሪያ ወጣ

ADDIS_NEWSneutral2026-09-27 11:50:50 UTC
AdYour ad here[email protected]

ለመንግሥት ትምህርት ቤት መምህራን የደረጃ ዕድገት አዲስ መመሪያ ወጣ ​የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚገኙ መምህራን የደረጃ ዕድገት ለማግኘት የሚያስችላቸውን አዲስ መመሪያ ደነገገ። ​የተማሪዎች ውጤት ማለፊያ መስፈርት፦ መምህራን የደረጃ ዕድገት ከሚያገኙባቸው ዋና ዋና ሁኔታዎች አንዱ ከሚያስተምሯቸው ተማሪዎች መካከል ቢያንስ 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ማሳለፋቸው በገለልተኛ አካል ሲረጋገጥ ብቻ መሆኑ በመመሪያው ተሰፍሯል። ​ሌሎች የምዘና መስፈርቶች፦ የተማሪዎች የትምህርት ውጤት እንዳለ ሆኖ፤ ተተግብረው ውጤት ያመጡ ጥናትና ምርምሮች እንዲሁም ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የተደረገ እገዛ ለደረጃ ዕድገት እንደ ዋና ዋና መስፈርቶች ተቀምጠዋል። @Addis_News @Addis_News

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]