የካታር መንግሥት በኢትዮጵያ ፌዴራል ኃይሎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ መካሄዱን በመግለጽ ድርጊቱን አወገዘ።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-09-27 13:23:11 UTC
AdYour ad here[email protected]

የካታር መንግሥት በኢትዮጵያ ፌዴራል ኃይሎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ መካሄዱን በመግለጽ ድርጊቱን አወገዘ። የኢትዮጵያ ፌዴራል ኃይሎች ላይ የተፈጸመው ድርጊት የሀገሪቱን አንድነትና ሉዓላዊነት እንዲሁም የአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋጋት ላይ የከፋ ሥጋት መደቀኑን ገለጿል። ወታደራዊ ውጥረቱን እና ጠብ አጫሪ ድርጊቶችን በአስቸኳይ ማቆም፣ ሲቪሎችን መጠበቅ እንዲሁም የፕሪቶሪያን የሰላም ስምምነት አክብሮ መንቀሳቀስ አስፈላጊ መሆኑን የኳታር መንግሥት አፅንዖት ሰጥቷል። ውጥረቱን ለማርገብና አለመግባባቶችን በንግግር እና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ለሚደረጉ ጥረቶች ሁሉ የኳታር መንግሥት ሙሉ ድጋፉን እንደሚሰጥ አረጋግጧል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]