ጃፓን ህወሓት/TPLF ወስዷል ያለችውን ወታደራዊ እርምጃ እንደምታወግዝ ገለጸች።
ጃፓን ህወሓት/TPLF ወስዷል ያለችውን ወታደራዊ እርምጃ እንደምታወግዝ ገለጸች። የጃፓን መንግሥት በሰሜናዊ ኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን የጸጥታ ሁኔታ አስመልክቶ ጥልቅ ስጋቱን ገልጿል። ህዝባዊ ወያኔ ሓነት ትግራይ (TPLF) በክልሉ የሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎችን መቆጣጠርን ጨምሮ የወሰዳቸውን ወታደራዊ እርምጃዎች አውግዟል። ሁሉም አካላት ወታደራዊ ውጥረትን እንዲያረግቡና አለመግባባቶችን በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቅርቧል። በተጨማሪም እ.አ.አ በ2022 የተፈረመው የፕሪቶሪያ ስምምነት መከበርና ተግባራዊ መሆን ወሳኝ መሆኑን የገለጸው የጃፓን መንግሥት በአፍሪካ ህብረት (AU) የሚመራውን የሰላም ድርድር ሂደት እንደሚደግፍ አሳውቋል። ሁኔታውን ከሚያባብሱ ድርጊቶች በመቆጠብ ለተጎዱ ወገኖች የሰብአዊ እርዳታ እንዲደርስም አሳስቧል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም…
Read the full story at tikvahethiopia ↗