“ ለኢትዮጵያ ክብር አለን ” ፓትሪክ ቬይራ
“ ለኢትዮጵያ ክብር አለን ” ፓትሪክ ቬይራ “ ስታዲየሙ እና ሜዳው በጣም ጥሩ ነው ” የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፓትሪክ ቬይራ ከነገው የኢትዮጵያ ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። አሰልጣኝ ፓትሪክ ቬይራ በሰጡት ቃል “ ነገ የምንጫወተው ለሶስት ነጥብ ነው “ ሲሉ ተናግረዋል። ፓትሪክ ቬይራ አክለውም “ ለኢትዮጵያ ትልቅ ክብር አለን “ ሲሉ ገልጸዋል። የኢትዮጵያን የመጨረሻ ጨዋታ መመልከታቸውን የገለፁት ቬይራ “ የተደራጀ እና ሚዛኑን የጠበቀ ቡድን ነው የምንገጥመው ” ብለዋል። ስለ ባሕር ዳር ስታዲየም ያነሱት አሰልጣኝ ፓትሪክ ቬይራ “ ሜዳው በጣም ጥሩ ሜዳ ነው ” ሲሉ አድንቀዋል። Via tikvahethsport #ዳጉ_ጆርናል
Read the full story at zena24now ↗