ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ግጭት ካለበት የትግራይ ክልል 161 ሰዎችን ወደ ሌላ ሥፍራ ማዘዋወሩን አስታውቋል።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-09-28 19:48:34 UTC
AdYour ad here[email protected]

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ግጭት ካለበት የትግራይ ክልል 161 ሰዎችን ወደ ሌላ ሥፍራ ማዘዋወሩን አስታውቋል። ዛሬ ሰኞ መስከረም 18/2019 ባወጣው መግለጫ ከትግራይ ክልል ካስወጣቸው መካከል ፦ - የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት እና ቤተሰቦቻቸው፣ - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው፣ - የሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ሠራተኞች፣ - የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢዎች እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አባላት ይገኙበታል። ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ፤ 161ዱን ሰዎች ከትግራይ ያዘዋወረው " ሁሉም የሚመለከታቸው ኃላፊዎች ባቀረቡት ጥያቄ እና በሰጡት ይሁንታ መሠረት፣ የገለልተኛ ሚና በመወጣት " እንደሆነ መግለጹን ቢቢሲ ዘግቧል። መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]