ከደህንነት ስጋት ጋር ተያይዞ በየመን በአንድ ሳምንት ውስጥ 16ሺ የሚጠጉ ዜጎች ተፈናቀሉ፡፡

ZENA24NOWneutral2026-09-29 14:41:19 UTC
AdYour ad here[email protected]

ከደህንነት ስጋት ጋር ተያይዞ በየመን በአንድ ሳምንት ውስጥ 16ሺ የሚጠጉ ዜጎች ተፈናቀሉ፡፡ በየሳምንቱ ያላቸውን ነገር በሙሉ ጥለው የሸሹ በሺዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ዜጎችን እንቆጥራለን ሲሉ በየመን የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል፡፡ በሀገሪቱ ምዕራባዊ የባህር ዳርቻ እና በደቡባዊ ክፍሎች ያለው የደህንነት ስጋት መቀጠሉን ተከተሎ ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ በየመን ወደ 16ሺ የሚጠጉ ሰዎች መፈናቀላቸውን ድርጅቱ ሰኞ ዕለት ይፋ አድርጓል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፍልሰተኞች ኤጀንሲ ባወጣው መግለጫ በሰኔ ወር በምዕራባዊ ዳርቻ ላይ ውጊያው ከተባባሰ ወዲህ በስምንት ግዛቶች ውስጥ 145ሺ 308 ዜጎች ወይም 24ሺ 218 አባወራዎች ተፈናቅለዋል። ይህም ቁጥር እ.ኤ›አ ከመስከረም 21 እስከ ሰኞ እለት ድረስ ከ12 በመቶ በላይ ጭማሪ አሳይቷል። በየመን የ…

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]