24 የመማሪያ ክፍል መስኮቶችን የሰረቁ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ

AYUZEHABESHANEWSneutral2026-09-29 16:38:25 UTC
AdYour ad here[email protected]

24 የመማሪያ ክፍል መስኮቶችን የሰረቁ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ በምዕራብ ጎጃም ዞን በቡሬ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ የቡሬ አቦ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማሪያ ክፍሎች 24 መስኮቶችን በመስረቅ የተከሰሱ ሦስት ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በእስራት መቀጣታቸው ተገልጿል። የቡሬ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ያየህ አድገህ እንደገለፁት የትምህርት ቤቱ አመራሮችና የአካባቢው ሕብረተሰብ ለፖሊስ ባቀረቡት ጥቆማ መሠረት ፖሊስ ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪዎቹን ለመያዝ ችሏል። ተከሳሾቹ የሰረቁትን መስኮቶች በባጃጅ ጭነው ወደ አዊ ዞን ቲሊሊ ከተማ በመውሰድ ለቁራሌ ለመሸጥ ሲሞክሩ መሆኑን ጥቆማ ከደረሰው በኋላ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ታኅሣሥ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ማድረጉን ኢንስፔክተሩ ገልጸዋል።…

Read the full story at ayuzehabeshanews ↗
AdYour ad here[email protected]