በአፋር ክልል በደረሰ የድሮን ጥቃት የክልሉ መንግስት መቀመጫ ተመታ

ADDIS_NEWSneutral2026-09-30 05:57:41 UTC
AdYour ad here[email protected]

በአፋር ክልል በደረሰ የድሮን ጥቃት የክልሉ መንግስት መቀመጫ ተመታ በተፈፀመዉ ከባድ የድሮን ጥቃት የክልሉ መንግስት መቀመጫ ቤተ መንግስት ግቢ ወስጥ ትላንት ምሽት 1:45 ገደማ ጥቃት መፈፀሙን ተሰምቷል ፡፡ ይህ ለክብር እንግዶች (VIP) እንዲሆን ታስቦ እየተሰራ ያለ ህንፃ ተመትቶ በእሳት መያያዙ የታወቀ ሲሆን ስለደረሰው ጉዳት እስካሁን አለመታወቁን ምንጮቻችን ጠቁመዋል። "በቦታው ከፍተኛ የፀጥታ ሀይል ተሰማርቶ የክልል ፕሬዚዳንቱን የመጠበቅ ስራ እየተሰራ ነው፣ ወደ ቦታ ሰው እንዳይደርስ እየተከለከለ መሆኑንም አይተናል" በማለት ምንጮች ለመሰረት ሚዲያ ተናግረዋል። ኤርፖርቱ በመደበኛ ስራው ላይ ነው፣ በረራም አልተቋረጠም። በዚህ መረጃ ዙርያ እስካሁን ከአፋር ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መረጃ የለም። @Addis_News @Addis_News

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]