#ችሎት

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-09-30 14:32:31 UTC
AdYour ad here[email protected]

#ችሎት ​በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የኢሕአፓ አባላት የዋስትና ጉዳይ ዛሬም ውሳኔ ሳያገኝ ለአርብ ተቀጠረ። ​የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት የሰጠው የዋስትና ውሳኔ ሊጸና ይገባል ወይስ አይገባም? እንዲሁም ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም? የሚሉትን ነጥቦች ለመመልከት የፌደራል ፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንዲቀርብለት ማዘዙ ይታወሳል። ​ይሁን እንጂ ሰኞ ዕለት በዋለው ችሎት "መዝገቡን እየተመለከትን ነው፣ አላጠቃለልንም" ያለው ፍርድ ቤቱ፤ በዛሬው ዕለት ደግሞ የስር ፍርድ ቤት ዋስትና የፈቀደበት ሰነድ (Hard Copy) እንዲቀርብለት በማዘዙ ምክንያት ብያኔ ሳይሰጥ ቀርቷል። ​በዚህም መሰረት ችሎቱ የሚቀርቡለትን ሰነዶች መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለመጪው አርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ​ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተጠርጣሪዎች አቶ…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]