ሳምንታትን ያስቆጠረው የመብራት ሃይል አገልግሎት መቆራረጥ

ZENA24NOWneutral2026-09-30 16:13:00 UTC
AdYour ad here[email protected]

ሳምንታትን ያስቆጠረው የመብራት ሃይል አገልግሎት መቆራረጥ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች የመብራት አገልግሎት ለማግኘት ነዋሪዎች እየተቸገሩ ይገኛል ። በተለይም በኮልፌ እና አዲስ ከተማ ክ/ከተሞች በስፋት ይህ ችግር ይስተዋላል ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎቱ የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት በመቋረጥ ላይ እንደሚገኝ ጠቁሟል ። አገልግሎቱን እስኪስተካከል በፈረቃ ሃይሉን ለማዳረስ እየጣረ እንደሚገኝ ጠቅሷል ። ሆኖም አሁንም ችግሩ በዘላቂነት ካለመፈታቱም ባሻገር ፣ በአግባቡ በተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ አልያም ፈረቃ ህብረተሰቡ አገልግሎት እያገኘ አይደለም ። #ዳጉ_ጆርናል

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]