"ሌ/ጀ ታደሰ ወረደ ለኤርትራ ተላልፈው ሊሰጡ ነው" — ጃዋር መሐመድ
"ሌ/ጀ ታደሰ ወረደ ለኤርትራ ተላልፈው ሊሰጡ ነው" — ጃዋር መሐመድ በመቀሌ በቁም እስር ላይ የሚገኙት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ እና ሌሎች የትግራይ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ወደ ኤርትራ ድንበር ከተማ አሰናብ ሊተላለፉ መሆኑን ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ ገለጹ። ዝውውሩ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር በተደረገ ስምምነት መሠረት የሚፈጸም ነው ተብሏል። በዚህ ዝውውር ውስጥ ከሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ፣ በተጨማሪ አቶ ኢሳይያስ ታደሰ፣ ኮሎኔል ተወልደ እምበብ እና ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር ዓለምሰገድ ይካተታሉ። አቶ ጃዋር አሰራሩ በሕይወታቸው ላይ ከባድ አደጋ የሚያስከትል በመሆኑ የተባበሩት መንግሥታት፣ የአፍሪካ ሕብረት እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት አስቸኳይ የሕይወት ዋስትና እና ከለላ እንዲሰጧቸው ጥሪ አቅርበዋል። ጄኔራል ታደሰ ወረደ ከወራት በፊት…
Read the full story at addis_news ↗