አዲስ አበባ‼️
አዲስ አበባ‼️ ትናንት በአዲስ አበባ የተሰማውን ፍንዳታ ተከትሎ አዩዘሀበሻ ከበርካታ ምንጮች ለማጣራት ሞክሯል። ትናንት መስከረም 20/2019 ዓ.ም ከለሊቱ 6:20 እና 7:20 ላይ ሶስት ጊዜ የድሮን ጥቃት መፈፀሙን ምንጮቻችን ለአዩዘሀበሻ አረጋግጠዋል። ድሮኖቹ ትናንሽ እና አጥፍቶ ጠፊ የሚባሉት አነስተኛ ድሮኖች ናቸው። አንደኛው መከላከያ ዋናው ቢሮ፣ሁለተኛው ቂርቆስ አራተኛው ሰፈር ሶስተኛው ቤተመንግሥት አከባቢ ነው። በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም፣ በንብረት ላይ መጠነኛ ጉዳት አድርሰዋል። መኪኖች በጣም ተጠጋግተው እንዳይቆሙ ምክረ ሃሳብ መሰጠቱን አሽከርካሪዎች ገልፀውልናል። Via : አዩዘሀበሻ @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Read the full story at addis_reporter ↗