“ሕወሓት በሀገር ላይ ከፍተኛ ክህደት ፈጽሟል”
“ሕወሓት በሀገር ላይ ከፍተኛ ክህደት ፈጽሟል” የትግራይ የሰላም ተልዕኮ አስተባባሪ ሌተናንት ኮሎኔል ገብረዋሕድ ኃይሉ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ ሕገወጡ የሕወሓት ቡድን ከውጭ ኃይሎችና ከሀገር ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመተባበር በሀገር እና በሕዝብ ላይ ከፍተኛ ክህደት ፈጽሟል። የቡድኑ የ30 ዓመታት የፖለቲካ ውድቀት ትግራይን የጦርነት አውድማ በማድረግ ሕዝቡን በማያባራ የኢኮኖሚ ውድቀት፣ የሥነ ልቦና ስቃይ እና ማኅበራዊ ውጥንቅጥ ውስጥ እንደከተተው ተመላክቷል። በትግራይ ክልል ያለው ወቅታዊ ምስቅልቅል የቡድኑን የባንዳነት እና የፖለቲካ ከንቱነት የሚያሳይ መሆኑን ያስታወቁት ሌተናንት ኮሎኔሉ፣ ሕዝቡ ለፍትሕና ለዲሞክራሲ የከፈለው መስዋዕትነት ወደ ባርነት መቀየሩን ገልጸዋል። ይህንን የቁልቁለት ጉዞ ለመቀልበስ ከዜሮ በመነሳት የፖለቲካ ምኅዳሩን፣ የሲቪል ማኅበራትን እና የሥነ…
Read the full story at addis_reporter ↗