የበጎ አድራጎት ፈርጡ አቶ ወንዱ በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
የበጎ አድራጎት ፈርጡ አቶ ወንዱ በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንዱ በቀለ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። እድሜያቸው በሰባዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የሚገኘው አቶ ወንዱ በካንሰር ያጡትን የልጃቸውን ማቲዎስን ስም በመሰየም እ.ኤ.አ. በ2004 ፋውንዴሽኑን ከመሰረቱበት ጊዜ ጀምሮ፣ ደሞዝ ከሚከፈላቸው የመንግሥት የኃላፊነት ቦታቸው በፈቃደኝነት በመልቀቅ ህይወታቸውን ሙሉ ለበጎ አድራጎት ሰጥተዋል። ፋውንዴሽኑ ላለፉት 22 ዓመታት ከ5,000 በላይ የካንሰር ህሙማንና ቤተሰቦቻቸውን የህክምና፣ የትራንስፖርት፣ የምግብና የሥነ-ልቦና ድጋፍ አድርጓል። በተጨማሪም በአገር አቀፍ ደረጃ የካንሰርና የትምባሆ ቁጥጥር ፖሊሲዎች እንዲወጡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ…
Read the full story at addis_reporter ↗