እናት ባንክ የመጀመሪያውን የሥርዓተ ፆታ ቦንድ ለገበያ ለማቅረብ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መሆኑን ገለጸ

TIKVAHETHMAGAZINEneutral2026-10-05 20:38:49 UTC
AdYour ad here[email protected]

እናት ባንክ የመጀመሪያውን የሥርዓተ ፆታ ቦንድ ለገበያ ለማቅረብ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መሆኑን ገለጸ እናት ባንክ በሴቶች ለተያዙና ለሚመሩ ኢንተርፕራይዞች የረጅም ጊዜ ፋይናንስ ለማቅረብ ያዘጋጀውን የሥርዓተ ፆታ ቦንድ/ Gender Bond ሽያጭ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ የባንኩ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አስቴር ሰሎሞን ገለጹ። ሰብሳቢዋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ እንደተናገሩት፣ የቦንድ ሽያጩን ለመጀመር የሚያስፈልጉ ጥናቶች ተጠናቀው የመጨረሻ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ብለዋል። የቦንዱ የመግዣ ዋጋ እና ወደ ሽያጭ የሚገባበት ትክክለኛ ቀን ቦንዱን ከሚያስተዳድረውና ከሚቆጣጠረው አካል ፈቃድ ሲገኝ የሚወሰን እንደሆነም ነው የጠቆሙት። ከዚህ የቦንድ ሽያጭ የሚሰበሰበው የፋይናንስ ምንጭ መደበኛ የብድር ዋስትና ማስያዣ ማቅረብ ለማይችሉ ሴቶች ብድር ለማቅረብ ከመዋሉም ባሻገር፣ ለፋይናንሺያል…

Read the full story at tikvahethmagazine ↗
AdYour ad here[email protected]