የዓዲግራት ከተማ ነዋሪዎች የኤርትራ (ሻዕቢያ) ጦር ሠራዊት ወደ ከተማቸው እንደገባ አሳወቁ።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-10-07 11:05:30 UTC
AdYour ad here[email protected]

የዓዲግራት ከተማ ነዋሪዎች የኤርትራ (ሻዕቢያ) ጦር ሠራዊት ወደ ከተማቸው እንደገባ አሳወቁ። የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ምድር፣ ትግራይ ክልል ወደ ምትገኘው የዓዲግራት ከተማ መግባቱን ነዋሪዎች ለጀርመን ድምጽ ሬድዮ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ፥ ወታደሮቹ ወደ መቐለ መስመር / አቅጣጫ ሲያመሩ እንደተመለከቱ ገልጸዋል። በመቐለ ከተማ የሚገኙ የመረጃ ምንጭ የኤርትራ ወታደሮች " በበርካታ ከባድ ተሽከርካሪዎች ተጭነው ወደ ደቡብ አቅጣጫ " እየተጓዙ መሆናቸውን በዓዲግራት ከሚገኙ ነዋሪዎች መስማታቸውን ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል። ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር በ40 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በምትገኘው ዓዲግራት የኤርትራ ወታደሮች እንደገቡ በተመሳሳይ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (AFP) ዘግቧል። ወታደሮቹ ከዓዲግራት በደቡባዊ አቅጣጫ ወደ መቐለ መስመር በመጓዝ ላይ እንደሚገኙ የዜና ወኪሉ…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]