በአዳማ ከተማ በሽርክና አብራት በምትሰራው ባልደረባዋ ላይ የአሲድ ውሀ የደፈችው ግለሰብ ተያዘች

ZENA24NOWneutral2026-10-07 14:20:49 UTC
AdYour ad here[email protected]

በአዳማ ከተማ በሽርክና አብራት በምትሰራው ባልደረባዋ ላይ የአሲድ ውሀ የደፈችው ግለሰብ ተያዘች በአዳማ ከተማ ደበላ ክፍለ ከተማ ኢሬቻ ቀበሌ በጋራ በመሆን ዳይመንድ የማሳጅ አገልግሎት አቋቁመው ሲሠሩ በቆዩ ሁለት ወጣቶች መካከል በተፈጠረ የገንዘብ አለመግባባት ባለደረባዋ ላይ የአሲድ ውሀ የደፈችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን የአዳማ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታውቋል። መብራቴ ጅሬኛ እና ኬርያ እንድሪስ የተባሉ ሃያዎቹ አጋማሽ ዕድሜ ላይ የሚገኙት ሁለቱ ወጣቶች ቀደም ሲል በነበራቸው የሥራ ልምድ ተነሳስተው በ2018 ዓ.ም ጥር ወር ላይ ገንዘባቸውን በማዋጣት ሥራውን ጀምረው በሂደቱም ስኬታማ በመሆን ሌሎች ሁለት ሴት ሠራተኞችን ጭምር ቀጥረው ሲሠሩ ቆይተዋል። ይሁን እንጂ ከስድስት ወራት ቆይታ በኋላ በገንዘብ ወጪ ዙሪያ አለመግባባት መፈጠሩን የአዳማ ከተማ አስተዳደር…

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]